ታሪክ
የባህርዳር ከተማ የተቆረቆረችው በ13ኛው ክፍለ ዘመን መግቢያ አካባቢ እንደሌሎች የኢትዮጵያ ክፍሎች ሁሉ ጣና ሐይቅና አካባቢዋ አዲስ በተነሳው ሰሎሞናዊው ሥርዎ መንግስት ወኪሎች መመራት እንደጀመረች መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፤በዙሁ ሥርዎ መንግስት ስሟም በዚያን ጊዜ ባህሩ ዳር ቤተክርስቲያን ለመስራት በመጡ አንድ ቄስ እንደተሰየመች ታሪክ ይነግረናል፡፡
በ1912 ዓ/ም አካባቢ በዚህች መንደር አሞሌ ጨውና ማሬ ትሬዛ ለመገበያያነት ይገለገሉ ነበር፡፡
በህር ዳር እስከ 1928 ዓ/ም አካባቢ በ3 መንደሮች ማለትም
- ካህናት መንደር
- ባላባት መንደር
- አስላም ሰፈር በተባሉ ሰፈሮች ተከፋፍላ ቆይታለች፡፡
የባህርዳር ከተማ በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ከሚገኙት ታላላቅ ከተሞች ውስጥ አንዷ ስትሆን በአጠቃላይ የቆዳ ስፋቱም 42160 ሄክታር ይጠጋል፡፡ ጂኦግራፊያዊ አቀማመጡም 11 ዲ 38 ሴ ሰሜን ላቲቱዩድ እና 38 ዲ10 ሴ ምስራቅ ሎንግቲዩድ መካከል ይገኛል፡፡ ከባህር ጠለል በላይ ያላት ከፍታ 1801 ሜትር ሲሆን ከተማዋ በጣና ሐይቅ ደቡባዊ ጫፍ ላይ የምትገኝና የጥቁር ዐባይ ወንዝ አቋርጧት ረጅሙን ጉዞ የሚጀምርበት በመሆኑ ልዩ ማራኪና ግርማ ሞገስ የተላበሰ የተፈጥሮ ገጽታ ተሰጥቷታል፡፡ ባህርዳርን በምስራቅ ተንታ፣ በደቡብ ሰባታሚት፣ በሰሜን ጣና ሃይቅና ወንጀጣ ቀበሌ እንዲሁም በምዕራብ ይባብ እየሱስ ያዋስኗታል፡፡ ከአዲስ አበባ በሰሜን አቅጣጫ 565 ኪ.ሜ ርቀት ላይ ስትገኝ በውስጧ ካላት የቱሪዝም ሃብት በተጨማሪ የሰሜን ኢትዮጵያ ቱሪስት መስህቦች ቀለበት (Northern Ethiopia historic route of movments) ዋነኛ ማዕከል ነች፡፡ ከተማዋ ተፈጥሮአዊ እምቅ የቱሪዝም ሃብት ያላት ከተማ ናት፡፡
ቋንቋ
ባህርዳር ከተማ 96.7 የሚሆኑ ነዋሪዎች የአማረኛ ቋንቋ የአፍ መፍቻ ቋንቋቸዉ ሲሆን ኦሮሞኛ ና ትግረኛ የአፍ መፍቻ ቋንቋ የሆነ ነዋሪዎች ይገኛል፡፡ይህም በፐርሰንት ሲገለፅ እንደ ቅደም ተከተላቸው 1.1 እና 0.98 ከጠቅላላው ቁጥር ይሸፍናል፡፡ ቀሪው ቁጥር በሌሎች የተለያዩ የቢሄርና ቢሄረሰቦች ቋንቋዎች የሚናገር ነው፡፡
የሃይማኖት ስብጥር
ከእምነት አኳያ 89.7% የኦርቶዶክስ ክርስቲያን ፣8.5% እስልምና ፣1.6% የፕሮቴስታንት አማኞች ይኖሩበታል ፡፡ ነዋሪዎቿ በብሄር ፣በእምነት፣ በአመለካከት፣በትምህርት ደረጃ ፣በገቢና በሌሎች በርካታ ጉዳዮች ቢለያዩም ተከባብረው፣ ተቻችለው፣ተፈቃቅረው ሀይማኖታዊ እና ሀገራዊ በአላትን ያከበሩ በሃዘን ፣በደስታእና በችግር ጊዜ እየተደጋገፉ እየተረዳዱና እየተጠያየቁ ለብዙ አስርት አመታት ኑረዋል ወደፊትም ይኖራሉ፡፡ /ምንጭ፡ ከሚያዚያ 2010 ዓ.ም ውቢቷ ባህር ዳር ከሚል መረጃ መፅሃፍ የተዎሰደ/
የህዝብ ብዛት
እንደ በርካታ የሀገራችን ከተሞች ሁሉ የባህር ዳር ከተማ ነዋሪዎች ቁጥርም በየአመቱ በከፍተኛ ሁኔታ እየጨመረ መምጣቱን በተለያዩ ወቅቶች የተደረጉ የቆጠራ ውጤቶች ያሳያሉ፡፡በየጊዜው የተደረጉ የህዝብ ቆጠራዎችን ስንመለከት በ1976 ዓ.ም በተካሄደው አንደኛ ዙር የህዝብ እና ቤቶች ቆጠራ 54 ሺህ 766 የነበረው በ1986 ዓ.ም በተካሄደው ሁለተኛ ዙር የህዝብ እና ቤቶች ቆጠራ ወደ 94 ሺህ 235 ከፍ ሊል ችሏል፡፡
የ1999 ዓ.ም የህዝብ ና ቤቶች ቆጠራን ውጤት ለይ በመመስረት የ2012 ዓ.ም በ5 ዓመት የዕድሜና በነጠላ ዕድሜ እንዲሁም በጾታ የተተነበየው የባህርዳር ከተማ አስተዳደር የህዝብ ብዛት 414763 ሲሆን ከዚህ ውሰጥ በገጠር የሚኖረዉ 49421 ሲሆን በከተማ የሚኖረው ደግሞ 365342 ነው፡፡ ከዚህ ውስጥ የወንድ ብዛት 201904 እና ሴት ብዛት 212859 ነው፡፡ የህዝብ ጥግግቱ ደግሞ 0.12 ሰው በሄክታር እንደሚሆንይገመታል፡፡
ዘመን |
ጠቅላላ ህዝብ ብዛት |
በከተማ ቀበሌ ነዋሪዎች |
በገጠር ቀበሌ ነዋሪዎች |
||||
ወንድ |
ሴት |
ድምር |
ወንድ |
ሴት |
ድምር |
||
2010 ዓ.ም |
378299 |
159468 |
170179 |
329647 |
24777 |
23875 |
48652 |
2011ዓ.ም |
356757 |
138181 |
158352 |
296532 |
30658 |
29567 |
60225 |