በባሕር ዳር ሊከሰት የሚችለዉን የጎርፍ አደጋ ለመከላከል የሚያስችል ሥራ መሥራቱን የባሕር ዳር ከተማ አስተዳደር

በባሕር ዳር ሊከሰት የሚችለዉን የጎርፍ አደጋ ለመከላከል የሚያስችል ሥራ መሥራቱን የባሕር ዳር ከተማ አስተዳደር መንገድ ባለሥልጣን ጽሕፈት ቤት አስታወቀ።

,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,

የባሕር ዳር ከተማ አስተዳደር መንገድ ባለሥልጣን ጽሕፈት ቤት ከመጋቢት 2013 . ጀምሮ በከተማዋ የሚገኙትን ዋና ዋና የጎርፍ ውኃ ማስወገጃ ቦዮችን የመጥረግ ሥራ

መሠራቱን አስታውቋል።የባሕር ዳር ከተማ አስተዳደር መንገድ ባለሥልጣን ጽሕፈት ቤት ሥራ አስኪያጅ አዳነ ጌታነህ ክረምት ገብቶ የጎርፍ መጥለቅለቅ ከመከሰቱ

በፊት የጎርፍ ማፋሰሻ ሥራ 150 ባለሙያዎች ሲሠራ መቆየቱን አስረድተዋል።

ከዓባይ ወንዝ እስከ ጣና ሀይቅ 3 ነጥብ 8 ኪሎሜትር ያለው ዋና የጎርፍ ማስወገጃ ቦይ ጠረጋ ተደርጓል ብለዋል። ሥራውን ለማከናወን 1 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ

እንደተደረገበትም ገልጸዋል።የጎርፍ መጥለቅለቅ ምክንያ የቦዮች በቆሻሻ መሞላት በመኾኑ ኅብረተሰቡ የተገነባለትን ማፋሰሻ በአግባቡ መያዝ እንዳለበትም አቶ አዳነ

አሳስበዋል። "ኅብረተሰቡ በተገነባለት መንገድ አሸዋ ሲደፋ፣ ድንጋይ ሲከምር፣ እንጨት ሲፈልጥበት ይታያል" ያሉት ሥራ አስኪያጁ እነዚህ ድርጊቶች የጎርፍ መጥለቅለቅ

ምክንያት ስለኾኑ ጉዳት መምጣቱ በፊት ጥንቃቄ ሊደረግ ይገባል ብለዋል። ጽሕፈት ቤታቸው አሁን ላይ በግንባታ ምክንያት የተዘጉ ቦዮችን የመክፈትና ጎርፉ የተፈጥሮ

ይዘቱን ጠብቆ እንዲወርድ የማስተንፈስ ሥራ እየተከናወነ መኾኑንም አመላክቷል።የባሕር ዳር የተፈጥሮ የመሬት አቀማመጥ ለጎርፍ ተጋላጭ እንደመኾኑ ወቅታቂ

ሥራ ሳይኾን ዘላቂ መፍትሔ ያስፈልጋል ብለዋል። በመኾኑምከባሕር ዳር ዩኒቨርስቲ ጋር በመተባበር ዘላቂ መፍትሔ ለማምጣት እየሠሩ መኾኑን ጠቁመዋል።

Share this Post